ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር
ኑ ከኖህ ጋር
አብረን እንሻገር
በቀላሉ ለአገልግሎት ያመልክቱ
ነገን አሻግሮ ራዕይ በመመልከት፣
ዛሬ እንቆጥባለን ለተሻለ ስኬት።
በኖህ ያስቀመጥነው የቁጠባ ገንዘብ፣
እኛን ረድቶናል ወደፊት እንድናብብ።
አባል ይሁኑ
የሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- በሕግ መብቱ ያልተገደበ
- ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የኅብረት ሥራ ማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአሠራር ደንቦችን የተቀበለና ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
- የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1000፣ የ2 ዕጣ (ሼር) 2,000 ብር ጀምሮ መግዛት ይኖርበታል
- ቢያንስ በየወሩ ከ500 ብር ጀምሮ፤ መቆጠብ የሚችል መሆን አለበት
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ / መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል
- ሁለት ስድስት ወር ያልሞላው፥ ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዞ መገኘት አለበት
- የልጆች ቁጠባ ለመጀመር የሚያስፈልው የወላጅ ወይም የአሳዳጊ እና የልጁን ጨምሮ! ሁለት ስድስት ወር ያልሞላው፥ ጉርድ ፎቶ ከልደት ሰርተፍኪት ይዞ መገኘት አለበት


ብድር ይውሰዱ
ከሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር ብድር ለመጠየቅ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- ብድር ጠያቂዉ የማኅበሩ አባል መሆን አለበት
- አባል ሁኖ ሁለት ወራት መቆየት ይኖርበታል
- በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ልክ! ቁጠባውን ቀድሞ ወይም ብድሩን እስኪጠይቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሳያቆራረጥ የቆጠበ መሆን አለበት
- የገቢ ማስረጃ እና ዋስትና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
- የታደሰ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
- በቂ ዋስትና ማቅረብ አለበት
ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
የቁጠባ አገልግሎት
መደበኛ ቁጠባ ፣ የፍላጎት ቁጠባ ፣ የጊዜ ገደብ ቁጠባ ፣ የልጆች ቁጠባ ፣ የአስራት ቁጠባ ፣ የግዴታ ቁጠባ
የብድር አገልግሎት
በተወሰነ ጊዜ ቆይታ ተመላሽ የሚሆን እና ወለድ የሚያስከፍል ወይም የማያስከፍል
የስልጠናና የማማከር አገልግሎት
ለአባላቱ ግዜውን እና ወቅቱን የሚመጥን የተለያዩ ሥልጠናዎችን ይሰጣል
አጋሮቻችን

