የሐመረኖኅየገንዘብቁጠባእና_ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጥፍ ይረዳው ዘንድ ፤ ዘመናዊ ሲስተምን ለመጠቀም! ከአዲስ አበባው ኢ-ቴክ (E-Tech) ከተሰኘ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ጋር፤ ስምምነት አደረገ።
የኅብረት ሥራ ማህበሩ፤ ለደንበኞቹ ዘመናዊ አገልግሎትን! በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ፥ በፍጥነት እየሰራ ይገኛል። ሆኖም! የኅብረት ሥራ ማህበሩ በዘመናዊ መልክ ተግባራዊ የሚያደርገው ይህ ቴክኖሎጂ፥ የኮር ባንኪንግ አገልግሎት አሠጣጥ ይባላል፡፡
ቴክኖሎጂው! በቀላሉ አባላቶች የሚስተናገዱበት እና ባሉበት ሆነው መረጃዎችን ከማድረሱ በተጨማሪም፤ አባላቶች በእጅ ስልካቸው ላይ! በተጫነ አፕሊኬሽን በመጠቀም፤ ያስቀመጡትን የገንዘብ መጠን በይለፍ ቃላቸው ወዲያውኑ! የሚያውቁበት እንደሆነ ተገልጿል።
አዲስ እየተዘረጋ ያለው የኮር ባንኪንግ አገልግሎት! ለ ህብረት ሥራ ማህበሩ አባላቶች ቀላል፣ ምቹ፣ ቀልጣፋና ተመራጭ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ነው።
ይህ …በእንዲህ እንዳለ ታዲያ!
ቴክኖሎጂው፣ወደፊት ለአሠራር ሂደት ዝማኔ እና ለማህበሩ የዕድገት መስመር፣ ትልቅ ዋጋ እንዳለው አያጠያይቅም።
2017 ዓ.ም