አባል ይሁኑ

የሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር

አባል ለመሆን መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

  • 1

    አንድ አመልካች አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት የመመዝገቢያ ክፍያ 1,000 ብር (አንድ ሽህ ብር) መክፈል አለበት፣ ይህ ክፍያ የማህበሩን የታተመ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች ቅፆችን ክፍያን ያካትታል፡፡

  • 2

    ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በማንኛውም ሁኔታ ተመላሽ አይደረግም ወይም ለአባሉ ሌላ ጥቅም አያስገኝም፣

  • 3

    የኅብረት ሥራ ማህበር አባል ለመሆን ዝቅተኛውን 2 (ሁለት) የዕጣ መጠን መግዛት አለበት፡፡ ለገዛው ሙሉ የዕጣ መጠን ሠርተፊኬት(ወይም ደረሰኝ) ይሰጠዋል፡፡

  • 4

    አንድ አባል! በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 500 (አምስት መቶ) ሲሆን ይህን ቁጠባ ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

  • 5

    አባሉ ከኅብረት ሥራ ማህበሩ እስካልተሰናበተ ድረስ! ወለድ በሚያስገኝ ሆነ በወለድ አልባ ከተቀመጠው መደበኛ ቁጠባ በማንኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ አይችልም፤፤ ነገር ግን ለሎች የቁጠባ አይነቶችን እንደአስፈላጊነቱ በቸገረው ጊዜወጪ ማድረግ ይችላል፡፡ ይህም በማህበሩ በውስጥ መመሪያ በአንድ ጊዜ ወጪ የሚደረገው የገንዝብ መጠን ይወሰናል፡፡

  • 6

    አንድ አባል የማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን አንድ ወር ሳይቆጥብ ያሳለፈው ቁጠባ መጠን ካለ አንድ ወር የብድር ወረፋ ቅጣት ይቀጣል ፡፡ሁለት ወር ሳይቆጥብ ያሳለፈው ቁጠባ ሁለት ወር የብድር ወረፋ ቅጣት ይቀጣል፡፡ ሶስት ወር ሳይቆጥብ ያሳለፈው ቁጠባ መጠን ካለ አምስት ወር የብድር ወረፋ ቅጣት ይቀጣል፡፡አራት ወር ሳይቆጥብ ያሳለፈው ቁጠባ መጠን ካለ ስድስት ወር የብድር ወረፋ ቅጣት ይቀጣል

የሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር

ብድር ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

የማህበሩ አባል በማመልከቻ ሲጠይቅ

የአባሉ በተከታታይ የስድስት ወር እና ከዛላይ ቁጠባ እና እጣ መጠን መቆጠብ

አባሉ የሚበደርውን የብድር መጠን 35 በመቶ መቆጠብ ሲችል

አንድ አባል ለሚሰጠው ብድር የብድር አገልግሎት 1% እና የዋስትና ማቅረብ

የሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር

ከአባልነት ለመሰናበት ቅድም ሁኔታዎች

  • 1

    አባሉ የመልቀቂያ ጥያቄውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ የ30 ቀናት ለኅብረት ሥራ ማህበሩ በፅሑፍ ማመልከት አለበት

  • 2

    የሥራ አመራር ኮሚቴ የመልቀቂያ ደብዳቤ! በደረሰው ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መልስ መስጠት ይኖርበታል፤ የአባሉ የስንብት ጥያቄውም በሥራ አመራር ኮሚቴው የሚወሰን ይሆናል

  • 3

    አመልካቹ በኅብረት ሥራ ማህበሩ ዕዳ እንደሌለበት ተረጋግጦ! የቆጠበው ከለወለዱ ሊከፈለው ይገባል

  • 4

    አንድ አባል ያለበቂ ምክንያት! ከአንድ ዓመት በፊት ለመውጣት ቢጠይቅ የገዛው እጣ የሚመለስለት አመቱ መጨረሻ፥ የትርፍና ኪሳራ ኦዲት ከተደረገ በኋላ ትርፍም ካለው ድርሻው ተሰትቶት ኪራራም ከሆነ የሚደርስበት ኪሳራ ሸፍኖ በዕጣ የከፈለውን የገንዘብ መጠን ይዞ መውጣት ይችላል

  • 5

    ከኅብረት ሥራ ማህበሩ እንዲሰናበት በሥራ አመራር ኮሚቴ ውሳኔ የተሰጠው አባል የቁጠበው ቁጠባ ወሩ መጨረሻ ወለዱ ታስቦለት በተቀመተው በማህበሩ ውስት መመሪያ መሰረት የሚመለስለት ይሆናል