ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር በከፍተኛ ዕድገት አባላቱን እያገዘ ይገኛል፡፡

ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር በከፍተኛ ዕድገት አባላቱን እያገዘ ይገኛል፡፡

ድሬዳዋ    በአገራችን የሕብረት ሥራ ማኅበራት አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ትልቅ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ለአገር ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። ከእነዚህ ተለዋጭ የፋይናንስ ተቋማት መካከል በድሬዳዋ ከተማ በከፍተኛ የዕድገት መነቃቃት ላይ የሚገኘው ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር አንዱና ዋናው ነው።

 

ማኅበሩ አባላቱ ከሚያገኙት ወርሃዊ ገቢ ላይ የተወሰነውን ገንዘብ በመቆጠብ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲረዱ እና የቁጠባ ባህልን እንዲያዳብሩ ለማስቻል በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ተመሠረተ። ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እያሳየ የመጣውን ተአማኒነትና የፋይናንስ አቅም መሠረት በማድረግ በአሁኑ ወቅት የነቁ አባላቱን ቁጥር 1,725 በላይ ማድረስ ችሏል። በተጨማሪም ባለፉት 4 ዓመታት ከ9 ወራት የሥራ ጉዞው ውስጥ 110 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለአባላቱ በማሰራጨት የአባላቱን የኢኮኖሚ ዓቅም በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል።

 

ማኅበሩ 2020 . በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ከሁሉም መሰል የፋይናንስ ተቋማት በቀዳሚነት ተመራጭ የሆነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት የሚል ስትራቴጂካዊ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

 

አካታች እና ዘመናዊ የቁጠባ ዓይነቶች (Types of Accounts)

ሐመረ ኖኅ የአባላቱን ፍላጎት፣ እምነትና የሕይወት ዘይቤ መሠረት በማድረግ ወለድ የሚያስገኝ እና ወለድ አልባ የቁጠባ አገልግሎቶችን በስፋት ያቀርባል፦

  • የግዴታ ቁጠባ (Compulsory Saving) እያንዳንዱ አባል በየወሩ የሚያስቀምጠው መደበኛ የአባልነት ቁጠባ።

  • የፍላጎት ቁጠባ (Voluntary Saving)

    እንደ አባላቱ የገንዘብ ፍሰት ፍላጎት የሚቆጥቡትና በማንኛውም ጊዜ የሚንቀሳቀስ የቁጠባ ዓይነት።

  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ (Time Deposit) ገንዘብን በውል ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ በማስቀመጥ ከፍተኛ ወለድ የሚታሰብበት።

  • የልጆች ቁጠባ (Minor Saving) ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች የሚቀመጥ ብሩህ ተስፋ ያለው የአደራ ቁጠባ።

የማኅበሩ አባል ለመሆን የሚሹ ዜጎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች

ማኅበሩ አዲስ አባል ለመሆን ለሚፈልጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ምቹና ተደራሽ አሠራርን ዘርግቷል፦

  1. የመነሻ ዕጣ (Share) ግዥ፦ ቢያንስ 2 ዕጣ መግዛት (የአንድ ዕጣ ዋጋ 1,000 ብር ሲሆን፣ ጠቅላላ መነሻው 2,000 ብር ይሆናል)።
    • ልዩ ማሳሰቢያ፦ በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ አባላት፣ 1 ዕጣ (1,000 ብር) በቅድሚያ ከፍለው፣ ቀሪውን ክፍያ አባል ከሆኑ በኋላ ባሉት 3 ወራት ውስጥ አጠናቀው እንዲከፍሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።
  2. የመመዝገቢያ ክፍያ፦ 1,000 ብር የአገልግሎት ክፍያ መክፈል።
  3. የዘወትር ቁጠባ፦ አባልነት ከተረጋገጠ በኋላ በየወሩ ቢያንስ 500 ብር የግዴታ ቁጠባን ሳያቋርጡ መቆጠብ።

ቀልጣፋና ደረጃውን የጠበቀ የብድር አገልግሎት አሰጣጥ

ማኅበሩ አባላቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ፣ የንግድ ሥራዎቻቸውን እንዲያስፋፉና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ሰፊ የብድር አማራጮችን በገንዘብ መጠን ከፋፍሎ አዘጋጅቷል፦

የብድር ዓይነት የብድር መጠን ገደብ (በብር)
አስቸኳይ ብድር እስከ 100,000 ብር ድረስ
የአጭር ጊዜ ብድር ከ100,001 እስከ 300,000 ብር ድረስ
የመካከለኛ ጊዜ ብድር ከ300,001 እስከ 600,000 ብር ድረስ
የረጅም ዓመት ብድር ከ600,001 እስከ 4,000,000 (4 ሚሊዮን) ብር ድረስ

 

📌 የብድር አገልግሎት ለማግኘት ሊሟሉ የሚገቡ ዋና ዋና ቅድመሁኔታዎች፦

  • በአባልነት ተመዝግቦ በተከታታይ ለ6 ወራት የቆጠበ።
  • ለሚጠይቀው የብድር መጠን ከ35% እስከ 40% የሚሆን የቁጠባ ክምችት በማኅበሩ ውስጥ ያለው።
  • የሚሰጠው የብድር መጠን አባሉ የቆጠበውን እስከ ሦስት እጥፍ (3 Times) ሊደርስ ይችላል (የሚፈቀደው ትክክለኛ መጠን ግን በእጣና በቁጠባው መጠን ላይ ተመስርቶ ይወሰናል)።

ይግቡ፣ ይቆጥቡ!

ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት ያለው የዕጣ (የአክስዮን) መጠን ውስን በመሆኑ፣ ፍላጎት ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ፈጥነው በመመዝገብ የዚህ ታላቅ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

📍 አድራሻችን፦ ድሬዳዋ / ሰይዶ / ከጋላክሲ ሆቴል ከፍ ብሎ

📞 ለበለጠ መረጃ በስልክ መስመሮቻችን ይደውሉልን፦ 0991670834

0991670835

የነገ ሕይወትዎን ብሩህ ለማድረግ፣ ዛሬውኑ ከሐመረ ኖኅ ጋር ይጓዙ!”