አገልግሎቶቻችን
የተለያዩ አገልግሎቶች
ማህበሩ ምን ምን አይነት አገልግሎቶችን ይሰጣል ...?
መደበኛ ቁጠባ
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበሩ በሚወሰነው የጊዜ ገደብ እና ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን መሰረት አባሉ በግሉ የወሰነውን የቁጠባ መጠን በተከታታይነት ያለማቋረጥ የሚቆጠበው ቁጠባ ነው፡፡
የፍላጎት ቁጠባ
አባሉ በፍላጎቱ ከመደበኛው ቁጠባ በተጨማሪ በተለያዩ የቁጠባ አይነት የሚቆጠበው ቁጠባ ነው፡፡
የጊዜ ገደብ ቁጠ
አባሉ በፍላጎቱ በተለየ የቁጠባ ወለድና በጊዜ ገደብ የሚቆጠብ የቁጠባ አይነት የሚቆጠበው ቁጠባ ነው፡፡
የልጆች ቁጠባ
እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑና በኅብረት ሥራ ማህበሩ የስራ ክልል የሚኖሩ ልጆች በቤተሰቦቻቸው በኩል የሚቆጥቡት የአደራ ቁጠባ አይነት ነው፡፡
የአስራት ቁጠባ
አባሉ በፍላጎቱ ከመደበኛው ቁጠባ በተጨማሪ በተለያዩ የቁጠባ አይነት የሚቆጠበው ቁጠባ ነው፡፡
የግዴታ ቁጠባ
አባሉ በግዴታ በተለያዩ የቁጠባ አይነት የሚቆጠበው ቁጠባ ነው፡፡
ብድር
አባላት ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ከገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ወይም ከፋይናንስ ተቋማት በሚደረግ ስምምነት መሰረት በተወሰነ ጊዜ ቆይታ ተመላሽ የሚሆን እና ወለድ የሚያስከፍል ወይም የማያስከፍል ገንዘብ ነው፡፡
የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
ለአባላቱ ግዜውን እና ወቅቱን የሚመጥን የተለያዩ ሥልጠናዎችን ይሰጣል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የኅብረት ሥራ ማህበር ታሪካዊ አመጣጥ፣ የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የንግድ ክህሎት ናቸው፡፡