ስለ ሐመረ ኖኅ

ሐመረ ኖኅ ማን ነው...?
ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥራ ማኅበር በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፤ የፌደራል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/09 መሰረት የተደራጀ ሲሆን! በዚሁ አዋጅ ቁጥር 46/08 አንቀጽ 36 ንዑስ አንቀጽ 6 መሰረት በነሃሴ 07 ቀን 2016ዓ.ም ዳግም ምዝገባ አድርጓል፡፡ ይህ የኅብረት ስራ ማኅበር ጽንሰትና ውልደቱ፥በሚያዚያ ቀን 12 2013 ዓ.ም 43(20 ሴቶች 23 ወንዶች) መስራች አባላቶች ጋር፤ አዲስ ነገርን ተጋፍጦ በማሸነፍ ለብዙዎች መትረፍ ችሏል፡፡
በ2020 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ ከሁሉም ተመሳሳይ ተቋማት በቀዳሚነት ተመራጭ የሆነ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማህበር ሆኖ ማየት
የአባላትን ፍላጎት መሰረት በማድረግ! ተደራሽና ፍትሀዊ የቁጠባና ብድር አገልግሎት በመስጠት፤የአባላትን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በስራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽኦ ማድረግና የቁጠባ ባህልን ማጎልበት ናቸው፡፡
የኅብረት ሥራ ማህበሩ አላማውን ከግብ ለማድረስ በሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ የሚከተሉት መርሆዎችን የተከተለ ነው፡፡
ሀ) አባልነት በፈቃደኝነትና በፍላጐት ላይ የተመሠረተና ለሁሉም ክፍት ነው፡፡
ለ) ዲሞክራሲያዊ አሠራር፣ አመራርና የውስጥ ቁጥጥር መከተል
ሐ) የአባላት ኢኮኖሚያዊ ተሣትፎ ማረጋገጥ
መ) ነፃና ራሱን በራሱ ማስተዳደር
ሠ) ተከታታይ ትምህርት፣ ሥልጠናና መረጃ መስጠት
ረ) ከሌሎች አቻ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር መተባበር
ሰ) ለአካባቢ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ጥረት ማድረግ
የኅብረት ሥራ ማህበሩና የአባላት የሚከተሉት እሴቶች አሉት፡
ሀ) ራስን በራስ መርዳት፣
ለ) የግል ኃላፊነትን መወጣት፣
ሐ) የዲሞክራሲ ባህል ማስፋፋት፣
ሠ) እኩልነት፣
ረ) ፍትሃዊነት፣
ሰ) ወንድማማችነት፣
ሸ) ታማኝነት፣
ቀ) ግልጽነት፣
በ) ተጠያቂነት
ተ) አሳታፊነት
ቸ) ማህበራዊ ኃላፊነት፣
አ) ለሌሎች ማሰብ ናቸው፣
የሐመረ ኖኅ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማህበር ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።
1) የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መደበኛና ሌሎች የፍላጎት ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት የአባላትን የቁጠባ ባህልን ማሳደግ፡፡
2) በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የተለያዩ የብድር አገልግሎቶች በመስጠት የአባላትን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማገዝ፤ በስራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽዖ ማድረግና የኢንቨስትመንት አቅምን በማጎልበት! እንደከተማና እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ማድረግ፡፡
3) የወለድና ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት የኢንቨስትመንት አቅምን ማጎልበት ፡፡
4) የአነስተኛ መድን ዋስትና ወይም የተካፉል አገልግሎት በመስጠት፥የአባላትን ቁጠባና ኅብረት ሥራ ማህበሩ ያሰራጨው ብድር ደህንነት በመጠበቅ ማህበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር ማስቻል፡፡
5) የፋይናንስ አገልግሎት አካታችነትን በማሳደግ፣ የኅብረተሰቡን የፋይናንስ ክህሎትና የቁጠባ ባህልን በማዳበር የአባላትን በራስ የመተማመን አቅም ማጎልበት፡፡
6) ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እና ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር የፋይናንስ ትስስር በመፍጠር የሚከሰተውን የፋይናንስ እጥረትና ክምችት ችግርን መፍታት፡፡
ሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
የቁጠባ አገልግሎት
መደበኛ ቁጠባ ፣ የፍላጎት ቁጠባ ፣ የጊዜ ገደብ ቁጠባ ፣ የልጆች ቁጠባ ፣ የአስራት ቁጠባ ፣ የግዴታ ቁጠባ
የብድር አገልግሎት
በተወሰነ ጊዜ ቆይታ ተመላሽ የሚሆን እና ወለድ የሚያስከፍል ወይም የማያስከፍል
የስልጠናና የማማከር አገልግሎት
ለአባላቱ ግዜውን እና ወቅቱን የሚመጥን የተለያዩ ሥልጠናዎችን ይሰጣል
የኛ ቡድን


