ብድር ይውሰዱ

የብድር ወለድ እና የብድር ዘመን
- ከአንድ ዓመት እስከ ሶስት ዓመት /36 ወራት/፤ ውስጥ ሥራ ላይ ውሎ የሚመለስ ብድር “የአጭር ጊዜ ብድር” ሲባል አምሰት ዓመት/60ወራት/ የሚወሰድ ብድር “የመካከለኛ ጊዜ ብድር” ይሆናል።
- ብድሩ የሚውልበት ተግባር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ አውሎ ለመመለስ የሚወስደው ጊዜ ከ15 ዓመት /180 ወራት/ የሚወሰድ ከሆነ “የረዥም ጊዜ ብድር” ተብሎ ይወሰዳል።
- ማኅበሩ ለተበዳሪው ብድሩን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ወለድ ያስባል፤ ተበዳሪውም የተበደረው ብድር ዋናውንና ወለዱን በየወሩ በተሰጠው የመመለሻ ጊዜ ይመልሳል።
- ማኅበሩ ለአበደረው የገንዘብ መጠን የአጭር ጊዜ ብድር በየዓመቱ ለሴቶችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አባላት 12% ለወንዶች 12.5%፤ የመካከላኛ ጊዜ 13% እና የረጂም ጊዜ ብድር 14% ወለድ ሆኖ የሚታሰበውም እየቀነሰ በሚሄደው(Amortization) በየወሩ በቀሪው ዕዳ ላይ ይሆናል።
- ማህበሩ ከሌሎች ከለጋሽና አበዳሪ ተቋማት የሚያገነውን ገንዘብ የሚያበድርበት የወለድ ተመን ማህበሩና ተበዳሪው በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት ይሆናል።
የሐመረ ኖኅ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር
ለአባላት የሚሰጥ የብድር አይነት፤ መጠን፤ የቁጠባ መስፈርት፤
የወለድ መጠንና የመመለሻ ጊዜ ገደብ
የብድር ዓይነት
-
አስቸኳይ የብድር አገልግሎት100,000 መቶ ሺህ35%35,000 (ሰላሳ አምስት ሺ)6 ወር እና ከዚያ በላይለሴቶችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አባላት 12% ለወንዶች 12.5%እስከ 75ሽ 1 ዓመት ከ75-100ሽ 2 ዓመት
-
ለአነስተኛ ንግድና ባህበራዊ አገልግሎት300,000 (ሶስት መቶ ሺ)35%105,000 (አንድ መቶ አምስት ሺ)6 ወር እና ከዚያ በላይለሴቶችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አባላት 12% ለወንዶች 12.5%3 ዓመት
-
ለባጃጅና ፎርስ ተሸከርካሪ አገልግሎት600,000 (ስድስትመቶ ሺ)35%210,000 (ሁለት መቶ አስር ሺ)6 ወር እና ከዚያ በላይ13 %5 ዓመት
-
ለቤትና ለስራ ተሸከርካሪ አገልግሎት2,500,000 (ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን)35%875,000 (ስምንት መቶ ሰባ አምስት ሺ)6 ወር እና ከዚያ በላይ13%5 ዓመት
-
ለቤት መስሪያና ማደሻ የብድር አገልግሎት4,000,000 (አራት ሚሊዮን)35%1,400,000 (አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን)6 ወር እና ከዚያ በላይ14%15 ዓመት